free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

በቀላሉ አትረታ


የሚያስጨንቃቸው ጉዳይ እጅጉን የቀለለ የሆነ ስንት እና ስንት የጭንቀት ጓዶች አሉ።
መናፍቃንን ተመልከታቸው ወኔያቸው እጅጉን የወረደ ፣ ቆራጥነታቸውም እጅጉን የበረደ ነው። አስተሳሰባቸውም እንዲህ ነው፦ በሙቀት ውስጥ አትዝመቱ ፤ ፍቀድልኝ አትፈታተነኝ ፣ ቤቶቻችን ጠባቂ የላቸውም ፣ አንዳች መከራ እንዳይደርስብን እንሰጋለን ፣ አሏህም ሆነ መልእክተኛው ማታለልን እንጂ አልቀጠሩንም........ወዘተ። እነዚህ አካላት ምንኛ የጠፉ ናቸው። ነፍሶቻቸውም ምንኛ የከፉ ናቸው። ጭንቀታቸው ሆዳቸው ፣ የምግቡ ሰሃኖች ቤቶችና ሰገነቶች ናቸው። ዓይኖቻቸውን ወደ ክብር ሰማያት ከፍ አላደረጉም ፤ ወደ ልቅና ኮከቦችም አልተመለከትኩም። የአንዳቸው የጭንቀትና የዕውቀት ጣርያ መሳፈሪያው (መጋለቢያው) ልብሱ ጫማውና የሚበላው ምግብ ነው። ወደነዚያም እጅግ ብዙ ሰዎች ተመልከት ቀን ማታ የመጨነቃቸው ምክኒያት ከሚስታቸው ወይም ልጃቸው ጋር አለመስማማት ከቅርብ ወዳጅ ጋር መጣላት እንግዳ የሆነን ቃል መስማት ወይም ቦታ የማይሰጠው ቀላል ችግር ስላጋጠመው ነው። የነዚህ ሰዎች የጭንቀት መንስኤዎች እነዚሁ ናቸው። ጊዜያቸውን የሚያሳልፉበት ላቅ ያለ ዓላማ የላቸውም ፤ ትኩረታቸውን የሚሰጡት መልካም ስራ አያውቁም። እንደተባለውም «ከኩባያ ውስጥ ውሃ ከወጣ አየር ይሞላል።» ስለዚህ የምትጨነቅለትና የምትተክዝለትን ጉዳይ ልብ ብለህ ተመልከተው። ይህ ሁሉ ጭንቀትና ድካም ይገባዋል ወይ? ምክኒያቱም አእምሮህን ፣ ደምህን ፣ እረፍትህንና ጊዜህን ሰጥተኸዋል። ይህም ትልቅ ኪሳራ ነው። የስነ-ልቦና ሐኪሞች እንደሚሉት «ለሁሉም ነገር የሚገባውን ልክ ስጠው» ከዚህ አባባላቸው ደግሞ የአሏህ ንግግር ይበልጣል።



«አሏህ በእርግጥ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ልክን አድርጓል»

ስለዚህ ለነገራቶች የሚገባቸውን ቦታ ፣ ሚዛንና ልክ ስጣቸው። በደልና ድንበር ማለፍን ግን አደራ። እነዚያ ደጋግ ሶሃቦች የነበራቸውን ጭንቀት ስንመለከት ዛፊቱ ስር ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር የሚያደርጉትን ቃልኪዳን መሙላት ነበር። ከዚያም የአሏህን ውዴታ አተረፉ ከነሱ መሃል ደግሞ አንድ ሰው ነበር የግመሉ ነገር አሳስቦት ሲጨነቅ ቃልኪዳን አምልጦት እነሱ ያተረፉትን የአሏህ ውዴ አጥቶ ቁጣን አተረፈ። ስለዚህ ወራዳ ነገሮችን ተዋቸው ፤ ቦታ አትስጣቸው ፤ ጭንቀትህ ተወግዶልህ ደስተኛ ሆነህ ራስህን ታገኘዋለህ።


351

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


XtGem Forum catalog